‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 393 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 393 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 12 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 393 ወንዶች ሲሆን ከተመላሾች መካከል 71 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ‎መስከረም 5/ 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 20 ሺህ 617 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

Please follow and like us: