የጡት ካንሰር የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል ቅንጅታዊ አሠራር እንዲጠናከር ተጠየቀ

በወዳጅነት አደባባይ የጡት ካንሰር የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስገንዘብ ያለመ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

‎‎በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የጡት ካንሰር የሴቶችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ሕመም መሆኑን ተናግረዋል። ‎ችግሩን ለመቀነስም ግንዛቤ ማስጨበጫን ጨምሮ ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። ‎የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎችም የጡት ካንሰር የሚያስከትለውን ማኅበራዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ሁሉም የድርሻውን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል።‎በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ9 ሺህ በላይ ሴቶች በጡት ካንሰር ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Please follow and like us: