የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዓለም አቀፍ የሕጻናት ቀንን በማስመልከት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ እንደሚገኝ ተገለፀ።

በክልሉ የህፃናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም ህፃናት” በ ሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ36ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የህፃናት ቀን እየተከበረ ነው።

‎ሁነቱን ምክንያት በማድረግ ‎ በወላይታ ዞንና በጋሞ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ተቋማት የማህበረሰብ የህፃናት ማቆያን/community day care/ ጉብኝትና ክትትል ተካሂደዋል ። በጉብኝቱ ‎ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ የተመራ ልዑካን በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ እና በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ የህፃናት ማቆያና የቅድመ ልጅነት ዕድገት (ECD) ማዕከል ጉብኝትና ክትትል አካሂደዋል ። ‎የህፃናት ማቆያዎች እናቶች የራሳቸውን ስራ ያለ ስጋት እንዲሰሩ ከማገዙም በተጨማሪ ህፃናቱ እንክብካቤና ጥበቃ እየተደረገላቸው ከእድሜ አቻዎቻቸው ጋር እየተጫወቱ የሚማማሩበት ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ወ/ሮ ካሰች በምልከታው ወቅት ተናግረዋል።

‎በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ በቡጋ ወንቼ ቀበሌ የቅድመ ልጅነት ዕድገት (ECD) ማዕከል እና በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ በሴፍትኔት ፕሮግራም የተሰራው የህፃናት ማቆያ ማዕከላት ቆላ ሙልአቶ ፣ ያይቄ እና ኦሞ ላንቴ በ3ቱም ቀበሌያት ጉብኝትና ክትትል አድርገዋል ። በጉብኝቱ የክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የቢሮ ም/ኃላፊ፣ የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ኃላፊ፣ የክልሉ ባለሙያዎች እና የሁለቱም ዞንና ወረዳ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
‎

Please follow and like us: