የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት ዘርፍ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የምስጋናና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

‎ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላትና ተቋማት የምስጋናና የእውቅና መርሐግብር አዘጋጅቷል። ‎ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሚኒስቴሩ ጋር ማህበረሰቡን በተለይም ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ‎ፕሮጀክቶቹ በመንግስትና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከርና በጋራ አብሮ መስራት ከተቻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ መሆናቸው ተጠቅሷል።

‎በተጨማሪም ሴቶችን ብቻ ተሳታፊ በሚያደርገው የቅድሚያ ለሴቶች የ5ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የንቅናቄ ስራዎችን በጋራ ሲያካሂድ መቆየቱን በማስታወስ ሚኒስቴሩ ላሳየው አጋርነት እውቅና ተበርክቷል።

Please follow and like us: