‎”ጥቃትን የማይታገስና የሚፀየፍ ማህበረሰብ በመፍጠር ለሁላችን የምትመች ሀገር እንገንባ፤ ጥቃትን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት የሚጠበቅብንን ሃላፊነታችንን እንወጣ” – ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ “ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 16ቱ ቀናት አለም አቀፍ የፀረ ፆታዊ ቀን አስመልክቶ ጋዜጣዊ ሰጥቷል።

‎በመግለጫው፥ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤእጎጌ ተስፋዬ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈጸም ጥቃት ድርብርብ ችግሮች የሚያስከትልና በሀገር ላይ አሉታዊ ተፅዕና የሚያሳድር በመሆኑ አስተሳሰቡም ሆነ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባል ብለዋል። ‎ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ አሰራሮችንና የአገልግሎት ስርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ እያደረገና በተጎጂዎች ላይ የሚደርሰውን የጤና፣ የማህበራዊና የስነ-ልቦና ጉዳት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‎የህግ ክፍተቶችን ለማረም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የንቅናቄ መርሐግብሩ ዋና ዓላማም ጥቃትን ለመከላከል፣ ተጋላጭነትን ለመቀነስ፣ ለተጎጂዎች ምላሽ ለመስጠትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራትን በተደራጀ አግባብ ለማከናወን እንደሆነ ገልፀዋል።

‎የንቅናቄ መርሐግብርን ለማቀጣጠል ብሔራዊ ሎጎ መዘጋጀቱንና እሰከታች ድረስ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመው ለስኬታማነቱ ተገቢው ክትትልና ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን አስታውቀዋል። ጥቃትን መከላከል የሁላችን ሃላፊነት የሁላችንም ምርጫ ሊሆን ይገባል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ጥቃትን የማይታገስና የሚፀየፍ ማህበረሰብ በመፍጠር ለሁላችን የምትመች ሀገር እንገንባ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

Please follow and like us: