በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት የቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን በአካባቢው ካሉ የመሰረታዊ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ሂደት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር መስራት ይገባል ተባለ፡፡

ይህ የተጠቀሰው በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት በሚተገበርባቸው ክልልና ከተሞች ስር ለሚገኙና በቀጥታ ተሳትፎ ለሚያደርጉና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መዋቅሮች ስር ለሚገኙ ማህበራዊ ባለሙያዎችና አመራሮች ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ነው።

በዕለቱ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጹት በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት የቋሚ እና ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ በሚሰጡ አገልግሎቶች የማስተባበር ሂደት ላይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር የሚያስችል እውቀት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊኖር እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ በተለይም የቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን በአካባቢው ካሉ የመሰረታዊ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ሂደት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖርና ህብረተሰቡን ተደራሽ ለማድረግ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት የቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን ሁለንተናዊ ሁኔታ መረጃ በማደራጀትና ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ የተሻለ ግንዛቤ እና የአፈፃፀም እምርታን ማሳየት ከሰልጣኞቹ እንደሚጠበቅም አጽእኖት በመስጠት አሳስበዋል፡፡ ስልጠናው የማህበረ ስነ ልቦናዊ ድጋፍ( Psyco social Support) አገልግሎቶች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ለተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚችሉበትን አቅም በማጎልበትና በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ለቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ ዘርፍ የስርዓተ ፆታ አካቶ ትግበራ (Gender & Social Development) እንዲሁም የማህበራዊ አገልግሎቶች ትስስር ላይ ትኩረት በማድረግ ተሰጥቷል፡፡

Please follow and like us: