‎ሚኒስቴሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሚዘጋጀው 70ኛው አለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ ቅድመ ውይይት መድረክ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ እንግዶች የክብር ‎መስተንግዶና የስጦታ ስነስርዓት አካሄደ

‎በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሚዘጋጀው 70ኛው አለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ የሴቶችና ማህበራዊ፣ የስርዓተ ፆታና ወጣቶች ሚኒስትሮችን ያሳተፈው ቅድመ ውይይት በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በመካሄድ ላይ ነው።

ውይይቱ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አስተባባሪነትና በተባበሩት መንግስታት የስርዓተ ፆታና ሴቶችን ማብቃት ድርጅት (UNWOMEN) ድጋፍ ነው አየተከናወነ የሚገኘው።
‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም ለመርሃ ግብሩ ተሳታፊ እንግዶች ልዩ የክብር የእራት ግብዣ ስነስርዓት በአራዳ ፓርክ አካሂዷል። ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ጊዜም፥ ለእንግዶች ስጦታ አበርክተዋል።


‎
‎

Please follow and like us: