Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የማህበራዊ ልማት ኃላፊነትን መወጣት ለመንግስት ብቻ የሚተው ኃላፊነት እንዳልሆነ ተጠቆመ
ይህ የተገለፀው ቢላሉ ሀበሻ የማህበረሰብ ልማትና ድጋፍ ማህበር የበጎ አድራጎት ድርጅት ምስረታ ለ25ኛው “የደግነት እና የሰብዓዊነት ዓመት” በሚል መሪ ቃል ባከበሩበት ወቅት ነው።

በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ እንደገለፁት እንደ ቢላሉ ሐበሻ ሀገር በቀል ድርጅቶች በሀገር ውስጥ መስፋፋት የማህበራዊ ኃላፊነትን በጋራ እና በቅንጅት ለመወጣት ያስችላል ብለዋል። የማህበራዊ ልማት ለአንድ አካል በተለይም ለመንግስት ብቻ የሚተው ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ የሚጠይቅ ስራ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሀገራዊ አቅምን በማሰባሰብ የሀብት ማሰባሰብን ሂደትን በማጠናቀር የግል ኩባንያዎች እና በማህበረሰብ ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች በራስ አቅም ሀብቶችን በማሰባሰብ፣ ሀገር በቀል የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመጠቆም እና በውጭ እርዳታ ላይ ጥገኝነትን ለመቀነስ የሀገር ውስጥ አጋር አካላት በቅንጅት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

እነዚህ ሰው ተኮር ስራዎችም ዜጎችን በጊዚያዊነት ከመደገፍና ከማገዝ ባለፈ ዜጎች በቋሚነት የሚታገዙበትን ብሎም ከራሳቸው አልፎ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው ስርዓትን መቀየስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መ/ቤቱም ከመሠል ተቋማት ጋር ትስስሩን በማጠናከር ማህበረሰቡን በሚጠቅሙ ዘላቂ ዘዴዎችን በመፍጠር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።y
