የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ በመቐለ ከተማ ለተገኙ እንግዶች አቀባበል ተደረገ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጲያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን በቅንጅት በሀገራችን ለ33ኛ ጊዜ ለሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀንን አስመልክቶ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት አመራሮች፣ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሠሩ ጋዜጠኞች ፣ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ አካል ጉዳተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመቐለ ከተማ ሲገቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማህበራዊ ጉዳይና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ፣ የቱሪዝምና ባህል ቢሮ፣ የክልሉ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ህብረት አመራሮች በጋራ በመሆን ነው።

ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ፤ Fostering disability inclusive societies for advancing social progress! ” ወይም “አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት – ለተሻለ ማህበራዊ ዕድገት!” በሚል መሪ ቃል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተናጋጅነት በመቐለ ከተማ ህዳር 24/2018 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በድምቀት ይከበራል፡፡

Please follow and like us: