ሚኒስቴሩ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተካታችነት፣ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተለያዩ የአሠራር ማዕቀፎችና ሰነዶችን በማዘጋጀት ለትግበራውም እየሠራ ይገኛል።

በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የትግራይ ክልል ማህበራዊ ጉዳይና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረስላሴ ታረቀኝ እንደገለፁት ቀኑን ቆጥሮ ከማክበር በዘለል የአካል ጉዳተኞችን ፖለቲካዊ ማሃበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ቃል የምንገባበት ቀን መሆን አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ አባይነህ ጉጆ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር እንደገለፁት እለቱ አካል ጉዳተኞች መቻላችንን የምናሳይበት እለት መሆኑን ጠቅሰው መንግስት በህግ ማዕቀፍ የተደገፈ ድጋፍ ካደረገ (አካታችነት) ከዚህ በተሻለ አገርን መጥቀም እንደሚችሉ ገልፀዋል ። አካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታና እድል ከተሰጣቸዉ ዉጤታማ ፍሬያማና አምራች ዜጎች እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም መንግስትና ግብረሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊዉን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም በዓሉን አስመልክቶ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በፓናሉ ሚኒስቴር መስሪያቤቱን በመወከል የተሰሩ ስራዎችን ያቀረቡት አቶ አለማየሁ ማሞ እንደገለፁት ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ ፖሊሲ የመጨረሻ ቅርፅ በማስያዝ እንዲፀድቅ ለውሳኔ ሰጭው አካል ማቅረብ እና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሆኑ ገልፀዋል ። ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች መብት አዋጅን በመከለስ እንዲፀድቅ ለውሳኔ ሰጪ አካል ማቅረብ፣የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ማሰልጠኛ ማንዋል፣ የምልክት ቋንቋ ማሰልጠኛ ማንዋል፣ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት የድጋፍ አሰጣጥና ክትትል የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ማካተቻ፣ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የኮሙኒኬሽንና የአድቮኬሲ ረቂቅ ማንዋሎችን አጠናቆ ለትግበራ ዝግጁ እንዳደረገ ጠቁመዋል ።

በተጨማሪም የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞች ፕሮቶኮል እና የኢትዮጵያ ጀግኖች የጦር አካል ጉዳተኞች ደንብ እንዲጸድቁ መከታተል እና የአድቮኬሲ ስራዎችን መስራት ላይ በስፋት እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ። በፓናል ውይይቱ ላይ ከግብርና ሚኒስቴር ፣ከላይት ፎር ዘወርልድ፣ ከትግራይ ክልልማህበራዊ ጉዳይና መልሶ ማቋቋም ቢሮ የተውጣጡ ባለሙያዎች የሚሠሩ አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የምግብ ዋስትና ፣ የአካል ጉዳተኞች በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ለአካል ጉዳተኞች ወጣቶች የኢኮኖሚ ስልጣን እንዲሁም በትግራይ ክልል የአካል ጉዳተኞችን ማካተት ላይ የተሠሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

Please follow and like us: