Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 611 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 611 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 269 ወንዶች እና 314 ሴቶች እንዲሁም 28 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 73 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 27 ሺህ 722 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
Please follow and like us:
