የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስኮፐስ የስልጠናና የማማከር ሃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት እና ኮሚኒቲ ኬር ኢንሼቲቭ ከተባለ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

‎የስምምነቱ ዋና አላማ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን በመከላከል፣ መደበኛ የሆነው ፍልሰት ለልማት አስተዋጽኦ በሚያደርግበት ጉዳዩች ዙሪያ እና ተያያዥነት ባላቸው ሥራዎች በትብብርንና ቅንጅታዊ ለመስራት እንደሆነ የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ገልፀዋል።

‎‎በተጨማሪም የምርምር ትብብርን፣ የጋራ ፈጠራን እና አቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማበረታታት፣ የቴክኒክ ዕውቀትንና የአካዳሚክ የጥናት ውጤቶችን ለመለዋወጥ፣ ዘላቂ ማኅበራዊ ተጽዕኖ ለማምጣት እንዲሁም በመንግሥታዊ፣ በግል እና በሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

‎ሚኒስቴሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በሴቶችና በወጣቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ግንዛቤ በመሰረታዊነት ለመለወጥ የሚያስችሉ የመከላከልና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በጋራ እየሰራ ይገኛል፤ ወደፊትም ይህንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Please follow and like us: