Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለአካል ጉዳተኞች የተሻለ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።
በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው በሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ ገልፀዋል።
ይህ የተገለፀው ሰክሰስ ፕላስ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው። በዕለቱ ክብርት ሁሪያ እንደገለፁት መሠል ድጋፎች የአካል ጉዳተኞችን ችግር ከማቃለል ባሻገር ሀገሪቱ ያላትን የሰው ሀይል ተጠቅመን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል። በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እያጋጠሙ ባሉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ የአካል ጉዳተኞች ደህንነት አደጋ ላይ የሚወድቅበትና ለችግር የሚጋለጡበት ሁኔታን ለመከላከልና ለመቀነስ መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአካል ጉዳተኞችን መብት የማስከበር ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ የሁሉንም ኃላፊነት ይጠይቃል ብለዋል። ሚኒስቴር መስሪያቤቱም ድጋፎች የታለመለትን አላማ እንዲያውሉ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ። የሰክሰስ ፕላስ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው በበኩላቸው ድርጅቱ ከተመሠረተ ሁለት አመት ያስቆጠረ ቢሆንም የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን በተለይም ዊልቸር በመስጠት ላይ እንዳለ ጠቁመዋል። የተጀመሩ ድጋፎችንም ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።
