Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ኢትዮጵያ ለሴቶችና ህፃናት ደህንነት ዋስትና የምትሰጥ የፍትህና የእኩልነት ተምሳሌት ሀገር እንድትሆን ሁሉችንም በጋራ እንስራ -ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ
ኢትዮጵያ ለሴቶችና ህፃናት ደህንነት ዋስትና የምትሰጥ የፍትህና የእኩልነት ተምሳሌት ሀገር እንድትሆን ሁሉችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ተናገሩ።
ክቡር ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት “ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪቃል ለ16 ተከታታይ ቀናት ሲከሄድ የቆየው የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀናት የንቅናቄ የማጠቃለያ መርሐግብር ላይ ነው። ጥቃት የማህረሰባችንን እሴቶች ይሸረሽራል፤ የሀገርን እድገት ግስጋሴ ይገታል፤ የማደግና የመለወጥ ፍላጎትና አቅምንም እንደሚጎዳ ገልፀዋል። የስነልቦና ጉዳት በመፍጠርም ጤናማና በራስ የሚተማመን ትውልድም ያሳጣናል ብለዋል። እንዲህ አይነቱን ፅዩፍ ተግባር ለመከላከል ለማስቆም የፍትህ ስርዓቱን ማዘመን፣ የተደራሽነትና የግልፀኝነት ልኬትን ማበጀት ይገባል ብለዋል። የፍትህ ተቋማት ጥቃት ለደረሰባቸው ዜጎች መተማመኛዎቻችን በመሆናቸው የችግሩን ውስብሰብት በመገንዘብ በፍጥነትና ባልተጓተተ አግባብ ጉዳያቸው እንዲታይ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ወንድች አጋርና ተሟጋች መሆን ይኖባቸዋል ያሉት ክቡር ፕሬዝደንቱ አጥፊዎችን ማረምና መገሰፅ ከመስመር የሚወጡና በፈፀሙት ጥቃት የሚኩራሩ ላይም አስተማሪ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ብለዋል።
እንደሀገር ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ድጋፍ ለመስጠት የአንድ ማዕከል አገልግሎትና ማረፊያዎችን ለማቋቋምና ለማስፋፋት ጥረት መደረጉ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብለዋል። ጎጂ ልማዶችንና የጥቃት አስተሳሰቦችን ከማስወገድ አኳያ የትምህርት ተቋማት ይህን ለማረጋገጥ ጤናማ የስርዓተ ፆታ አስተምህሮ እንዲኖር ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አሳስበዋል። የልብ ስብራት የሚጠግኑ የማህበረሰብንጰአስተሳሰብ በበጎ የሚያቀኑ በኪነጥበብ የታጀቡ ስራዎች ለህዝብ በማቅረብ እኩይ ተግባራትን ማውገዝ ያስፈልጋል ብለዋል። ግጭት በሚከሰትባቸው ወቅቶች ግጭትን ተንተርሰው ፆታዊ ጥቃቶችን ለደረሰባቸው የተቀናጀና መልሶ የማቋቋምና ምላሽ የመስጠት ስራ በትኩረት እንዲሰራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
