Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችን አቅም መገንባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማህበረሰብ እድገት ወሳኝ መሆኑን ተጠቆመ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የኤስ.ኤን ቪ (SNV) ኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑትን ጁሊያን ግራሃምን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይቱ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት የሴቶችን አቅም መገንባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማህበረሰብ እድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ዘላቂ የልማት ስራዎችም ይህንን ይበልጥ ለማጠናከር ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ የልማት ስራዎች በመተግበር ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱም በተለይም ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና ለችግር ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በዘላቂነት ማብቃት ላይ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኤስ.ኤን ቪ (SNV) ኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑትን ጁሊያን ግራሃም በበኩላቸው የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የህፃናት መቆያ ማዕከላት በማስፋፋት፣ ማህበራዊ አካታችነት፦ የአካል ጉዳተኞችን፣ ወጣቶችን እና ሴቶችን ያካተቱ የልማት ስራዎች በግልና በመንግስት ስርዓት ተዘርግቶላቸው መስራት እንዲቻል ድጋፍ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡
Please follow and like us:
