Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሥጋ ደዌ ተጠቂዎች በማህበራዊና እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የዕኩል ዕድልና ሙሉ ተሳትፎ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ እንሰራለን – ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ72ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ27ኛ ጊዜ ሚከበረው የዓለም ሥጋ ደዌ ቀን የሥጋደዌ በሽታን አንዘንጋው በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የተለያዩ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ፣የሻሸመኔ ከተማ ም/ከንቲባ፣ የኢትዮጲያ አካል
ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር ዳይሬክተርና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በመከበር ላይ ይገኛል።
በዕለቱ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የሚንስትር አማካሪ የሆኑት ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ እንዳሉት የስጋ ደዌ በሽታ ፈውስ ከተገኘ ወዲህ የመጣውን ለውጥ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ጠቅሰው በተገኘው መልካም ውጤት ሊይ በመመስረት ይበልጥ የጋራ ጥረት በማድረግ ቀሪ ችግሮችን ማስወገድ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሥጋ ደዌ ተጠቂዎች በማህበራዊና እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የዕኩል ዕድልና ሙሉ ተሳትፎ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። መንግስት የአካል ጉዳተኞችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ ክብርና ማህበራዊ ደህንነት ማስጠበቅ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውንናተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው ሚኒስቴሩም የስጋደዌ ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደርሰውን አድሎና መገለል እንዲወገድ ከግንዛቤና ንቅናቄ ስራዎች ባሻገር የኢትዮጵያ ሥጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሔራዊ ማህበርን በመደገፍ በቅንጅት መስራት ይገኝበታል ብለዋል።
ሥጋደዌን በተመለከተ የበሽታው ስርጭት አሁንም የሚስተዋል በመሆኑ ስለ በሽታው አጠቃላይ ሁኔታ ተገቢውን ውጤት ሊያመጣ የሚችል የተጠናከረ የግንዛቤ ሥራ በመስራትና በተለይ ስለበሽታው በቂ እውቀት ካለማግኘት የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ የተዛቡ አመለካከቶችን ማስወገድ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ሥጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሔራዊ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ከፍያለው በቀለ በበኩላቸው ማህበሩ ሥጋደዌን በተመለከተ የችግሩን ምንጭ ከስር መሰረቱ ለማድረቅ አባላቱ በግንባር ቀደምትነት በመደራጀት ስለ ሥጋ ደዌና ስለተጠቂዎች ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን አሁንም ችግሩን ለመቅረፍና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሁሉም ዜጎች ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
በዕለቱ በቀረቡት ፅሁፎች መሠረት የበሽታው ስርጭት በአሮሚያና አማራ ክልሎች 87% ሲሆን በሌሎች ክልሎች ደግሞ 13% መሆኑ ተጠቁሟል። በዓሉን አስመልክቶም በሻሸመኔ እና አካባቢዋ ላሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የስጋደዌ ተጠቂዎች የማዕድ ማጋራት፣ የአካል ድጋፍ መሣሪያዎች ድጋፍ ተደርጓል ።
