‎በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ትውልድን የሚቀርፁ እና ለህፃናት ምቹ ሁኔታ የፈጠሩ ናቸው- ክብርት ሒክማ ከይረዲን

‎የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይረዲንን ጨምሮ ከአፋርና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሴቶች አደረጃጀቶች የስራ ሃላፊዎች በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ተግባራትና ሌሎች የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

‎‎የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይረዲን ጉብኙቱን አስመልክተው እንደገለጹት፥ የኮሪደር ልማት ስራዎች የቅድመ ልጅነት እድገት ዘመን ፕሮግራሞችን በማሳካት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ለዚህም መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች የአረንጓዴ ልማትን ጨምሮ የህፃናት ማቆያዎችን፣ መጫወቻና መዝናኛ ስፍራዎችን የማስፋፋት ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
‎

‎በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችም ለቀዳማይ ልጅነት ዘመን ተግባራት ትኩረት የሰጡ መሆናቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ‎የኮሪደር ልማት ስራዎቹ ትውልድን የሚቀርጹ እና ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ምቹ ሁኔታ የፈጠሩ መሆናቸውን በመግለጽ የተጀመሩ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ክብርት ሒክማ ከይረዲን መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎

Please follow and like us: