Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለቀዳማይ ልጅነት ዘመን እድገትና ትምህርት ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ
Nየኢፊዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ከህፃናት አደን ድርጅት( save the children) ጋር በጋራ በመሆን በቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገትና ትምህርት ፖሊሲና ሌሎች የማስፈፀሚያ ማኑዋሎች ዙሪያ ከክልሉ ዞኖችና የከተማ አስተዳዳሮች ለተውጣጡ አስፈፃሚ አካላት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። በመድረኩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የትምህርት፣ ጤናና የከተማ ልማትና የመሠረተ ልማት እንዲሁም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች በመድረኩ በመገኘት የጋራ ኃላፊነትን ለመውሰድ ያላቸውን ቁርጠኛነት አሳይተዋል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ህፃናት ላይ መስራት ለነገ የሀገር ዕድገት መሠረት መጣል በመሆኑ ባለድርሻ አካላት አፅንኦት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የክልሉ መንግስት የቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገትና ትምህርት ፖሊሲ የተሳካ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣምና ተናግረዋል። የሚመለከታቸው ተቋማትም ለተፈፃሚነቱ የጋራ የድርጊት መርሀ-ግብር በመቅረጽ ተቀናጅትው ከመስራት ባሻገር ስራውን እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር በማውረድ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት መብት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ በበኩላቸው፥ መንግስት የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በተለይም ሀገራዊ የህፃናትን ሁለንተናዊ እድገትን በሁሉም ስፍራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የንቅናቄና የግንዛቤ ስራዎችን በመስራት የሚጨበጥ ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። የዛሬዎቹ ህፃናት በመልካም ስብዕና ለመቅረፅ፣ ለዕድገታቸው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችሉ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማውጣት እንዲተገበር መድረጉን መሪ ስራ አስፈፃሚዋ አብራርተዋል።መድረኩ እንደ ሀገር ብሔራዊ የቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገትና የትምህርት ፖሊሲ ማዕቀፍ መፅደቁን ተከትሎ የተለያዩ የማስፈፀሚያና የመከታታያ ሰነዶችን በማዘጋጀት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቃማት ኃላፊዎችና ባለሞያዎችን በማሰልጠን ስራውን በእውቀት እንዲመራና በክልሎች በሚገኙ የተዋረድ መዋቅሮችን ለማብቃትና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ የሚያግዝ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ የህፃናትን መብትና ደህንነት የማስጠበቅ ጉዳይ ለቤተሰብ ብቻ የሚተው አለመሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ከአገልግሎት ጥራትና ህግና መመሪያዎችን በአግባቡ ከመተግበር አንፃር ውስንነት መኖሩንና ስልጠናውም በዘርፉ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን እንደሚቀርፍ ገልፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ረገድ የገባውን ቃል በፍጥነት ምላሽ ስለሰጠ ምስጋና አቅርበዋል፡፡