Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የተባበሩት መንግስታት የስርዓተ ጾታ ድርጅት ( UN WOMEN) በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ሴት ድምጽ ሰጪዎችንና ሴት ተመራጮችን ለመደገፍ ዝግጁነቱን ገለጸ
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር) ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው አዲሷን የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ድርጅት የኢትዮጵያ ወኪል ጃኔት ኬም ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም ወቅት አዲሷን የኢትዮጵያ ወኪል አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ለኢትዮጵያ የአገልግሎት ጊዜያቸው ውጤታማነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትብብር እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በተጨማሪም ሚኒስትሯ የተቋሙን ስራዎች በተለይም የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና የፓለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ ያለውን ተግባራት ያስተዋወቁ ሲሆን በተለይም የሴቶችን የፓለቲካ ተሳትፎ እና ውክልና ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በተባበሩት መንግስታት የስርአተ ጾታ ድርጅት ወኪል ጄኔት ኬም በበኩላቸው ሴቶችን የፓለቲካ ተሳትፎ እና ውክልና የማረጋገጥ እና የሴቶች የኢኮኖሚ አቅምን ማብቃትን አስመልክቶ ተቋሙ የሚሰራቸው ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል በተለይም በመጪው ጠቅላላ ምርጫ የሴት ድምጽ ሰጪዎችንም ሆነ ተመራጮች ለማገዝ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
Please follow and like us:
