ቤተሰብን ለማጠናከር፣ ለህጻናት ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማብቃት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች እንዲበራከቱ ጥሪ ቀረበ

ይህ የተገለጸው በኤስ.ኦ.ኤስ አማክኝነት በስዊስ የገንዘብ ድጋፍ በሚተገበረውና  የቤተሰብን፣ የህፃናትን፣ የወጣቶችን እና የማህረሰብ ልማትን ዓላማ ባደረግ የፕሮጀክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጹት ቤተሰብ ተገቢ ሚናውን ለመወጣት በቤተሰብ ደህንነት እና በማህበረሰብ ማብቃት ላይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ በሚያደርጉ እንዲሁም የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ የተከተሉ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ በተለይም በህፃናት ጥበቃ፣ በቤተሰብ ደህንነት እና በማህበረሰብ ማብቃት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ቤተሰብን ለማጠናከር፣ ለህጻናት ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማብቃት የሚያስችሉ መሠል ፕሮጀክቶች እንዲበራከቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በፕሮጀክቱ በሚከናወኑ ተግባራት  የጤና፣ የትምህርት እና የኑኖ ሁኔታን ለማሻሻል የሚከናወኑ የፕሮጀክቱ ውጥኖች ቤተሰብ በራሱ አቅም ችግሮችን እንዲፈታ በእጅጉ የሚያግዙ በመሆናቸው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለትግበራው ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል ድርጅቱ ቤተሰብንና ማህበረሰብን ማጠናከር፣ እንዲሁም የህጻናትና ወጣቶችን ደህንነት ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑን አምኖ እንደሚሰራ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማርያም አበበ ገልፀዋል።

ፕሮጀክቶቹ በሚቀጥሉት ከሶስት እስከ አራት ዓመታት ውስጥ በሲዳማ ክልል (አለታወንዶ እና ይርጋለም) እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል (ያቤሎ) የሚተገበሩ ስድስት አዳዲስ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ማጠናከሪያ ፕሮጀክቶች ይፋ ሆነዋል።

Please follow and like us: