Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ስልጠናዎች በየደረጃው ላሉ አመራሮችና የፖለቲካ ሃላፊዎች ትኩረት በመስጠት የግንዛቤና የውይይት መድረኮች እንደሚመቻች ተገለጸ
ይህ የተገለፀው በአዲሱ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት አደረጃጀትና አሰራርን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 1105/2017 መሰረት የተቋቋሙት የግንዛቤ ፈጠራና የተጎጂዎች ጥበቃና ድጋፍ የስራ ቡድኖች የ2018 የመጀመሪያ ስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ የጋራ መድረክ ከአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው፡፡
የሚኒስቴሩ የህገውጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሾች ክትትልና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ተግይበሉ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና መደበኛ የሆነ ፍልሰት ለማበረታታት የሚያስቸል የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና ተያያዝ መመሪያዎችና የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና ለሚመለከታቸው የክልል ባለሙያዎች መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡ በቀጣይም በፍልሰት አስተዳደር በተመለከተ በወጡት ህጎችና መመሪያዎች፣ በአለም አቀፍ ስምምነቶችና አፈጻጸም፣ በብሄራዊ የቅብብሎሽ የአሠራር ስርዓት፣ በተግባቦት ክህሎትና ጽንሰ ሃሳብ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ/ መደበኛ ፍልሰትን ለማበረታት የተዘጋጀው የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ፣ ተጎጂ ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 969/2015 በየደረጃው ላሉ አመራሮችና የፖለቲካ ሃላፊዎች ትኩረት በመስጠት የግንዛቤና የውይይት መድረኮች እንደሚመቻች ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና የወንጀሉን አስከፊነት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር፣ ተጎጂ የሆኑ የፍልሰት ተመላሽን አግባብነት ካላቸው የክልልና የከተማ አስተዳደር ቢሮዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ አለም አቀፍ ድርጀቶችና ሀገረ በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል:: ተጎጂ ለሆኑ ዜጎችም አስፈላጊውን ማህበራዊ፥ ስነ-ልቦናዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ተግባራት እንዲያስተባብር እንዲያገኙ በማድረግ ወደ አካባቢያቸውና ቤተሰባቸው የመቀላቀል ስራን የማስተባበርና የመምራት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
የፍልሰት ተጎጂዎች ጥበቃና ድጋፍ የስራ ቡድን በአዲስ መልክ የተደራጀ በመሆኑ እስካሁን ስራውን ሲመሩበት በነበረበት ሁኔታ ላይ እና በቀጣይ ወራት በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ አቅደው ስለሚሰሩበትና ለስራ ቡድኑ በህግ ስለተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት ዙርያ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
