የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን በአንድ ቋት መመዝገብ የሚያስችል ብሔራዊ የዲጂታል ስርዓት ልማትና ትግበራ ላይ ምክክርና የአቅም ግንባታ ስልጠና ተካሄደ

የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን በአንድ ቋት መመዝገብ የሚያስችል ብሔራዊ የዲጂታል ስርዓት ልማትና ትግበራ ላይ ምክክርና የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተካሄዷል።

‎‎የሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጥበቃ ማሰተባበርያና መከታተያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ጀማል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎች መመዝገቢያ ስርዓት እንደ ሀገር ወጥና ትክክለኛ መረጃ እንዲኖር፣ ድግግሞሽን በማስቀረት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞችን አፈፃፀም እና ተፅእኖ ለመገምገም፣ የማሻሻያ ቦታዎችን በመለየት እና የአገልግሎቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ስርዓቱ ለማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ተጠቃሚዎች ማዕከላዊ የመረጃ ቋት ሆኖ የተጠቃሚዎችን መረጃ በትክክል የሚመዘግብ እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ውጤታማ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓቶችን ለማስተሳሰር ከማስቻሉም በተጨማሪ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ትክክለኛውን አገልግሎት ለተገቢው ተጠቃሚ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

‎የተጀራጀና አሁናዊ መረጃ በዘመናዊ መንገድ መያዝ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔ ለመወሰን የሚያስችል ግብዓት ለማግኘት ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል። በሰልጠናው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ባሉ በሴቶች፣ በህፃናት፣ በወጣቶች እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፍ የሚገኙ ፕሮግራሞችን የሚተገብሩ ሁሉም ስራ አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Please follow and like us: