‎ኢትዮጵያና ቺሊ በሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ ከቺሊ አምባሳደር እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ሮድሪጎ ኢዱራዶ ጉዝማን ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

‎‎በውይይቱም ክብርት ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን ሃላፊነት እና በየዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል። ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የሚያስችልም የአምስት አመት ብሔራዊ ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመው ቺሊ ድጋፏን እንድታጠናክር ጠይቀዋል። ‎አምባሳደር ሮድሪጎ ኢዱራዶ በበኩላቸው፥ ሚኒስቴሩ በየዘርፉ እየሰራቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀዋል። በቀጣይም በሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና ተያያዥ መስኮች ላይ አጋርነትን የበለጠ ለማጠናከር እና በትብብር ለመስራት የቺሊ መንግስት ዝግጁ እንደሆነ ገልጸዋል።

Please follow and like us: