Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ ለሚያከናውናቸው የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን ( ECD) ለመደገፍ ቻይልድ ፈንድ ቃል ገባ።
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከቻይልድ ፈንድ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ኢሳም ጋኒምን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ኢትዮጵያ የህፃናትን መብትና ደህንነት ለመጠበቅ ከመቼው ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየሠራች እንደሆነ ጠቁመዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም በአሁኑ ወቅት በህፃናት ጉዳይ አያያዝ በበይነ-መረብ የሚፈጸሙ የህፃናት ትንኮሳዎችን ለመከላከል እየሰራ መሆኑኔም ጠቁመው እነዚህ ስራዎችን የጋራ ጥረት የሚጠይቁ በመሆናቸው ከቻይልድ ፈንድ ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት አሳይተዋል።
ከቻይልድ ፈንድ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ኢሳም ጋኒም በበኩላቸው በሚኒስቴሩ በመከናወን ላይ ባሉ ስራዎች አንደተደነቁ ገልፀው ድርጅቱ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ከመቀጠል ባለፈ የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን (ECD) እንደሚደግፎ ቃል ገብተዋል ።
Please follow and like us:
