Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የወንዶች ተሳትፎ ጉልህ አስተዎፅኦ እንዳለው ተገለጸ
ለስርአተ-ፆታ እኩልነት የወንዶችን በምልዓት የማሳተፍ ብሔራዊ ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የወንዶች ተሳትፎ ጉልህ አስተዎፅኦ እንዳለው ገልፀዋል። ኢትዮጵያ በሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ላይ በተሻለ መልኩ እየሰራች መሆኑ የተረጋገጠ ሁኔታ ላይ ብትሆንም :: ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦችን በሚፈለገው መልኩ ለማሳካት ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ስትራቴጂው ሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም ፆታን መሠረት አድረገው የሚፈፀሙ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከልና በማስቆም ረገድ ወንዶች በጎ ሚናቸውን እንዲወጡ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ስለ ሴቶች እኩልነት ስናነሳ ከጀርባ ሆነው በተሟላ መንገድ የሴቶችን ስራ ይዘው በተሻለ መልኩ የሚሰሩ ወንዶች መኖራቸውን ጠቅሰው የሚዘጋጀው ስትራቴጂ አበርክቷቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያስችላል ብለዋል። የወንዶችን አጋርነት ለማሳደግ እንዲያስችል የተዘጋጀው የስትራቴጂ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተሳታፊዎች ያላቸውን ልምድና የሌሎች ሀገራትንም ተሞክሮ መነሻ በማድረግ ሊያሰሩ የሚችሉ ጠቃሚ ግብዓቶችን ሰጥተውበታል። በመርሀ-ግብሩ ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር፣ ከአፋር፣ ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከኦሮሚያ፣ ከጋምቤላ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከሀረሪ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከፌደራል እና ከልማት አጋር የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል። > የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር – Ministry of Women and Social Affairs: 🖼 Photo
