Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የተሟላ የህፃናት የቅድመ ልጅነት እድገት ስራን ማጠናከር ይገባል – ክብርት ሂክማ ከይረዲን
በፌዴራል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቅድመ ልጅነት ዕድገት (ECD) Steering Committee አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም በዋናነት ብሔራዊ ቅድመ የልጅነት እድገት መዳበር እና ትምህርት ፖሊሲ ማዕቀፍ ፣ ከቅድመ-ወሊድ ጀምሮ ዕድሜያቸው እስከ ሰባት ዓመት በሚሆናቸው ሕፃናት ላይ ያተኮሩ ፖሊሲዎችን ጨምሮ በዚህ የሕይወት ደረጃ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሕፃናት ጥራት ያለው ቀዳማይ የልጅነት እድገት፣ መዳበር እና የቅድመ-መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ በማስቻል ፣ አካላዊ ፣ ሥነ-ልቦናዊ ፣ አእምሯዊ እና ማህበራዊ እድገታቸውን እንዲጠናከር ለማድረግ እንደሚረዳም ተነስቷል። በእለቱም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን አምራችና በስነ ምግባር የታነፀ ዜጋን ለማፍራት የተሟላ የህፃናት የቀዳማይ ልጅነት እድገት ስራን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አፅኖት ሰጥተዋል። ሚንስትር ዴኤታዋ አክለውም ጥራት ያለው የቀዳማይ የልጅነት እድገት መዳበር ላይ የሚደረግ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት በዘላቂነት ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶችን ለመከላከል እንደሚያግዝና ሀገራችን ወደ ጀመረችው የብልፅግና ጉዞ ለመድረስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደደሚኖረውም ተናግረዋል።

የቅድመ ልጅነት እድገትና መዳበር ላይ መስራት የተለያዩ ሴክተሮችን ተሳትፎና ድጋፍ የሚፈልግ እንደሆነ የገለጹት ክብርት ሂክማ ባለድርሻ አካላትን በሰፊው በማካተት እና ከአለም አቀፍ እይታዎች ጋር በማስተሳሰር ስታንዳርዶችን የማሻሻል ስራ መስራት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም የተቋማት የህፃናት የቀን መንከባከቢያና ማቆያ (ዴይኬር) እናቶች ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ፣ ህፃናትም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት የገለፁት ክብርት ሂክማ ለመንግስት ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ዴይኬርን ማስፋፋት፣ የተከፈቱትን ስታንዳርዳቸውን ማሻሻልና ማሳደግ ፣ማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያን ማስፋፋት በማህበረሰቡ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና በራሳቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የሚሰሩ እናቶችን ለማገዝ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
በሲዳማ ክልል የቅድመ ልጅነት እድገት ፖሊሲ በአመራሩ እና በማህበረሰቡ ውስጥ አጀንዳ ተደረጎ መያዙ ጥሩ እንደሆነ አንስተው በቀጣይ ትግበራውም በተሻለ መንገድ መፈፀም እንዳለበት ከስትሪንግ ኮሚቴው ጋር ተግባቦት ተፈጥሯል::
በርሀግብሩም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ፣የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን በንግግራቸው ለህፃናት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ለነገ ትውልድ ምሶሶነው ብለዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን የህፃናት የቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገትና ትምህርት ፖሊሲ አተገባበርን አስመልክቶ የባለድርሻ አካለት ሚናና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
በርሀግብሩም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ፣ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
