የማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያዎች መስፋፋት የሴቶችን ጫና በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥም ባለፈ ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመገንባት ትልቅ ሚና ይኖረዋል – ክብርት ሒክማ ከይረዲን

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት በPFC ገንዘብ ድጋፍ የተገነባው ማዕከል ምርቃትና ስራ ማስጀመርያ  መርሀግብር ተካሂዷል።

‎የማህበረሰብ ዓቀፍ የቀን ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከሉ የተገነባው በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ ነው። ‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን የማህበረሰቡ የህፃናት መዋያና መንከባከብያ ማዕከል ትውልድ ለመገንባት፣ ትውልድ ለማነፅ፣ የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅዎ ያደርጋል ብለዋል። የማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያዎች መስፋፋት የሴቶችን ጫና በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥም ባለፈ ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመገንባት ትልቅ ሚና ይኖረዋል

‎ሚኒስቴሩ የህፃናትን መብት፣ ደህንነት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ የተቀረፀውን የቅድመ ልጅነት ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ በቅንጅት እተስራ መሆኑን ገልጸዋል። እንደሀገር 2ሺህ 500 የማህበረሰብ እና የተቋማት ዴኬር ተቋቁመው ከመቶ ሺ በላይ የሆኑ ህጻናትን  ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። የቅድመ ልጅነት ፕሮግራም ሁሉን አቀፍ ፕሮግራሞችን አቀናጅቶ የያዘ ስለሆነ ተቀናጅተን ትውልድን እንገባ በማለት አስገንዝበዋል።

‎‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ሀገራችን እንደ ፓርቲ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።  የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች የክልሉ መንግስት በሩ ክፍት ነው ያሉ ሲሆን ይህንንም ስራ ለፍሬ ለማብቃት ከፌደራል እስከ ክልል ብሎም PFC አስተባባሪ አካላት ምስጋናን አቅርበዋል። የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ የነገዋን ሀገር የሚረከቡ ህፃናት መብትና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ በጋራ ልንሰራ ይገባል በማለት ተናግረዋል።

‎የማዕከል ምርቃትና ስራ ማስጀመርያ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ መምህራን እና የአካባቢው ኑዋሪዎች ተገኝተዋል።

Please follow and like us: