Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የቤተሰብ እና የጉርብትና ህይወት ለሀገራዊ የጋራ ትርክት!!
ቤተሰብን ስናስብ ማህበረሰባዊ አብሮነትን ወይም የጉርብትና ሕይወትን ነጥለን ማየት አንችልም።ጎረቤት ለቤተሰብ ወሳኝ አጋር ነው። ጉርብትናውም ሊቀር የማይችል ትስስር ነው። ቤተሰብ ደስታምሆነ ሀዘን ሲገጥመው አስቀድሞ የሚሄደው ወደ ጎረቤት ነው። አንድ ቤተሰብ በጉርብትና ህይወቱ ውስጥ ደስታን ለመካፈል፣ ከሀዘን ለመጽናናት፣ ሽምግልና የሚያስፈልገውጉዳይ ሲኖር በምክክር እርቅ ለማውረድ፣ ልጆችን ለመጠበቅ እና ዕለታዊ የአደራ እንክብካቤ ለማድረግ ሊተባበር ይችላል።#ጥሩ_ጉርብትና_እንዴት_ይፈጠራል መልካም ጉርብትና ለመፍጠር፣ የቤትን እና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ፣ ከጎረቤት ጋር ንግግር እና ውይይት ማድረግ፣ አካባቢን እና ጎረቤትን ሊረብሹ የሚችሉ አላስፈላጊ ድምጾችን ማስወገድ፣ አስፈላጊጉዳዮችን ለጎረቤት ማሳወቅ፣ የህብረተሰቡን እሴቶች እና ደንቦች ማክበር ያስፈልገል።

የጉርብትና ህይወት የላላ ከሆነ መለያየት እና በችግር ጊዜ ያለመተባበር ሁኔታ ሊፈጠር ብሎምልዩነቶች ሲሰፉ፣ ግጭቶችም ሊከተሉ ይችላሉ። ስለሆነም የሚከተሉት ጉዳዮች የቤተሰብ እና የጎረቤት መልካም ግንኙነት ማዳበሪያ መንገዶችናቸው:-Ø እንደ እድር እና መሰል አደረጃጀቶች ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ፣Ø በአካባቢየጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ ውይይት ማድረግ፣Ø የአካባቢውንወይም የሰፈሩን ሰላም፣ ጽዳትና መሰረተ ልማት በጋራ መጠበቅ፣Ø ለልጆችምቹ የመጫወቻ ስፍራዎችን ማዘጋጀት፣Ø የባህል፣የሃይማኖት፣ የቋንቋ እና መሰል ልዩነቶችን ማክበር እና ልምድን መለዋወጥ ያስፈልጋል።# የሚከተሉት ጉዳዮች ጎረቤት ከጎረቤት ጋር በሚኖረው ግንኙነት ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ ጉዳዮችናቸው:-Ø የተዛቡየጉርብትና መረጃዎችን በጥንቃቄ መለየት እና ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ፣Ø በተለያዩሱሶች አካባቢውን ከመረበሽና የጎረቤት ልጆችንከሚጎዱ ድርጊቶች መቆጠብ፣በጎረቤትጉዳይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት ከማድረግ መቆጠብና የጎረቤትን ሁለንተናዊ ክብር መጠበቅ፣Ø ከማኅበ ራዊቅርርብ እራስን አለማግለል እንዲሁም በአካባቢው ተቀባይነት ያላቸውን የጋራ እሴቶች መጠበቅ፣Ø ከጎረቤትጋር ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ውስጥ ከመግባት መቆጠብ፣Ø ለጎረቤትየሚደረጉ መልካም ነገሮችን በውለታና በምላሽ እሳቤ አለማድረግ የሚሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ።ከጎረቤት ጋር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ግጭት ውስጥ ያልገባውን ሌላኛውን ጎረቤትእንዲሁም አረጋውያንን ወይም ሽማግሌዎችን በመጠቀም ማሸማገል፣ የተጣሉጎረቤታሞች ካሉ በዝምታ ከመመልከት ይልቅ ማስታረቅ እና ተኮራርፎ ለረጅም ጊዜያት የመቆየት ልምዶችን ማስወገድ ተገቢ ነው።በዚህ መልኩ ቤተሰብና ጎረቤት መልካም እሴቶችን ማስጠበቅ ሲችሉ ጤናማ ማህበረሰብ ብሎም የሚያግባባሀገራዊ የጋራ ትርክት የመገንባት ሂደት የተሳካ ይሆናል።
የ2018 የቤተሰብ ቀን “በመልካም ቤተሰብ፣ መልካም ትውልድ፣ ለፀና ሀገር!!”በሚል መሪ ቃል መከበሩ ይታወሳል፡፡
