Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ልዩ ፍላጎት ያላቸው ሕፃናት እንክብካቤና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ለአስፈፃሚ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከSOS Children’s village ጋር በመሆን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ሕፃናት እንክብካቤና ምላሽ አሰጣጥ እና የአፍሪካ የህፃናት ቀን ሀገራዊ እቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመርሀ-ግብሩም ከሁለቱ የከተማ አስተዳደርና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የፍትህ ቢሮ አስፈፃሚ አካላት ተገኝተዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህጻናት መብትና ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ በንግግራቸው የህፃናት አያያዝ ስርዓትን የማሻሻል በተለይም ደግሞ ለችግር ተጋላጭና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህፃናት መብትና ደህንነት ለማስከበር በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ልዩ ፍላጎት ለላቸው ሕፃናት እንክብካቤና ምላሽ እየሰጡ ያሉ አካላትን አመስግነው በቀጣይ በተጠናከረ አግባብ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የዘንድሮ የአፍሪካ ህፃናት ቀን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህፃናት እና ድጋፍ እየሰጡ ያሉ ቤተሰቦችንና ተቋማትን መደገፍና በማጠናከር ለህፃናት የተሻለ ተጠቃሚነት አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር እንደሚከበር ገልፀዋል። አስፈፃሚ አካላትን ግንዛቤውን በመውሰድ ለተግባራዊነቱ የማስተባበር ስራ መስራት ይጠበቅባችዋል ሲሉ ተናግረዋል። የረቂቅ ት/ትና ስልጠና መስጫ ተቋም ኃ/የተ/የግል/ ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ፍሬህይወት ይጨነቁ የግንዛቤና የአቅም ግንባታ ስልጠናው የሚፈለገው ለውጥ እንዲያመጣና ግቡን እንዲመታ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
