የፌዴራል የማህበራዊ ጥበቃ መድረክ (platform )3ኛ መደበኛ ስብሰባ ትኩረቱን ተጋላጭ ዜጎችን ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች በማድረግ ተካሄደ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመውን የፌዴራል የማህበራዊ ጥበቃ ፕላትፎርም ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባ በትላንትናው ዕለት አካሂዷል።

የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዕለቱ እንደገለፁትየፕላትፎርሙ መኖር ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ተጋላጭ ዜጎችን በተለይም ህጻናት፣አረጋውያን ፣ሴቶችንና ለተለያዩ ተጋላጭ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ጥበቃና ድጋፍ አግኝተው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ዘላቂ መሻሻል እንዲያሳዩ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።በተጨማሪም በሴፍቲኔት ፕሮግራም ውስጥ የቅድመ – መደበኛ ህጻናት እድገትን ማካተት እና ከአመጋገብ ስርዓት ጋር የተያያዙ ማህበራዊ ጥበቃ ስራዎች የተሠሩ ስራዎችን በመገምገም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና የህጻናት ደህንነት ማስጠበቅ በትኩረት እንዲሠ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም በውይይቱ ወቅት የሚነሱ ሀሳቦች መረጃ ከመለዋወጥ ባለፈ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና የተቀናጀ አሰራርን ባማከለ መልኩ ወደ ተጨባጭ ተግባርና ቀጣይ እርምጃዎች መሸጋገር እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል። በመድረኩ ካለፈው ውይይት ወዲህ የተመዘገቡ ስኬቶችን መገምገም እና ቀጣይ በማህበራዊ ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ስራዎችን በመዳሰስ ተጠናቋል

Please follow and like us: