የህፃናት የተሳትፎ መብት ለማረጋገጥ…

ባለፉት የለውጥ አመታት የህጻናት ፓርላማዎችን በፌዴራል እንዲሁም ከክልል መዋቅር ጀምሮ እስከ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ድረስ በማደራጀትና በማጠናከር ህፃናት ሃሳባቸውን በነፃነት መግለፅ፣ ራሳቸውን በሚመለከትጉዳይ ላይ በጋራ መምከርና የዴምክራሲን ባህል ማጎልበት እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
‎
‎የህፃናት ተሳትፎን ለማጎልበት በተካሄዱ አለም አቀፍና አህጉራዊ ኩነቶችና ፌስቲቫሎች እንዲሳተፉ፣ የህፃናት ክበባት እንዲቋቋሙ፣ የህጻናት አደረጃጀቶች ስልጠና እንዲወስዱ፣ የልምድ ልውውጥና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ የማጠናከር ስራ ተሰርቷል:: በህፃናት ፓርላማ አስተባባሪነት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ህጻናት በችግኝ ተከላና እንክብካቤ እንዲሁም አልባሳትና የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ አቅመ ለሌላቸው ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡

Please follow and like us: