Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ልጃገረዶችን የንፅህና መጠበቂያ ችግር ለመቅረፍ እና በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን ለስራ ብቁ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሴቶችና ልጃገረዶች ድጋፍ – ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሴቶችና ልጃገረዶችን የንፅህና መጠበቂያ ችግር ለመቅረፍ እና በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን ለስራ ብቁ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የመግባባቢያ ስምምነቱን የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የሴቶችና ልጃገረዶች ድጋፍ – ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙሉዓለም ታምሬ ናቸው የተፈራረሙት። የስምምነቱ ዋና አላማ ዘርፈ ብዙ ለሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች፣ ልጃገረዶች እና አካል ጉዳተኞች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ የተሟላ ስብዕናና የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ማስቻል እንደሆነ ተመላክቷል።
የንፅህና መጠበቂያ ሞዴልን ጨምሮ ፓዶችን ማከፋፈል የሚያስችል ዲጂታል ማሽን /Dispensing Machine/ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለዩኒቨርሲቲዎች ማቅረብ አንዱ የስምምነቱ አካል መሆኑ ተጠቅሷል። በተጨማሪም ለሴቶችና ልጃገረዶች የሙያ ክህሎት ስልጠና በመስጠት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለመቀነስና በተጠቃሚዎች ህይወት ላይ የሚጨበጥ ውጤት ለማምጣት የሚያግዙ ተግባራትንም በጋራ ለመስራት የስራ ሃላፊዎቹ ተስማምተዋል።
Please follow and like us:
