ዓለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ከውክልና ባለፈ ሴቶችን ተጠቃሚና እኩል ተሳታፊ የሚያደርጉ ስራዎችን ይበልጥ እንዲያጠናክር ተጠየቀ

በዓለም አቀፍ የሴቶች ዲፕሎማሲ ቀንን አስመልክቶ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልናን ወደ ሚታይና ተጨባጭ የውሳኔ ሰጪነት አስፈፃሚነት ላይ የተሠሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥን ማምጣታቸውን ጠቁመዋል።
ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ 41.3 በመቶ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ እና በፌዴራል ካቢኔ ውስጥ ሙሉ እኩልነትን በማስፈን ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ጠንካራ ምሳሌ እየሆነች መምጣቷን ገልጸዋል። ነገር ግን የሴቶች ውክልና አሁንም በክልላዊ ምክርቤቶችና ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን ከመያዝ አንፃር ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ዓለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ከውክልና ባለፈ ሴቶችን ተጠቃሚና እኩል ተሳታፊ የሚያደርጉ ስራዎችን ይበልጥ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

በቅርቡም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው አዲሱ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ-ፆታ እኩልነት ፖሊሲ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

Please follow and like us: