‎የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሴቶችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሴቶችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
‎‎በኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 90 ሚሊየን ለማድረስ ግብ መቀመጡ ይታወቃል። ‎የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በታህሳስ ወር  ”ፋይዳ ለሴቶች” ሀገር አቀፍ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብርን አስጀምሯል። ‎ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲን ለኢዜአ እንዳሉት፤ የሴቶችን የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠቃሚነት ለማላቅ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤትነትና ተደራሽነት በስፋት እየተሰራበት ይገኛል።
‎
‎ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበርም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሚገኝ መገለፁን ኢዜአ በዘገባውጠቅሷል።
‎

Please follow and like us: