‎የተሻሻለውን የሴቶች ማብቃትና ስርዓት ፆታና እኩልነት ፖሊሲ እና አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በሁሉም መስክ ያሉ ሴት አመራሮችንና ምሁራን በሳተፈና በየደረጃው ላሉ ሴቶች ተጨባጭ ውጤት በሚያመጣ መልኩ ወደተግባር እንዲቀየር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

የኢትዮጵያ ሴቶች ማብቃትና ስርዓተ-ጾታ እኩልነት ፖሊሲ የግንዛቤ መድረክ እና 50ኛ አመት የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማጠቃለያና የምስጋና መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

‎‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ ላለፉት 32 አመታት በስራ ላይ የቆየውና በቅርቡ የፀደቀው አዲሱ የሴቶች ማብቃትና የስርዓተ-ጾታ እኩልነት ፖሊሲ የሴቶችን ችግር ሊፈታና የተሻለ ተሳታፊና ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ተሻሽሎ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። ፖሊሲው የሴቶች የትግል ውጤት መሆኑን በስኬት ጠቅሰው የሀገራችን ሴቶች የተሻለ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየርና ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ክብርት ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል። ‎ሚኒስቴሩ ፖሊሲውን ለማስፈፀም የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፎች እያዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው ለስኬታማነቱ የግንዛቤ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ‎የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይሬዲን በበኩላቸው፥ የሴቶች እኩልነት ትግል የተጀመረበትና የሴቶችን መብት ለማስከበር ባለፉት 50 አመታት በተከናወኑ ተግባራት የተገኘውን ውጤት አስመልክቶ የተካሄደውን ሀገራዊ የንቅናቄ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።

‎‎50ኛው ዓመት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የእዮቤልዩ ክብረ በዓል ከአዳራሽ በዘለለ ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት በከፍትኛ የትምህርት ተቀማትን ያሉ ሴት ምሁራንን ወደፊት በመያመጣና በተሰማራበት መስክ ለሀገር የሚኖራቸውን አበርክቶ በሚያጎላ፣ የተጠናከረ ትብብርና ቅንጅት የታየበት እንደነበር አስታውሰው፥ የንቅናቄ መርሐ-ግብሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ላደረጉ አካላት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። ‎በዓሉን ምክንያት በማድረግ የፌዴራል ሴት አመራሮች በሁሉም ክልሎች ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከመምህራን፣ ከተማሪዎችና ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር በሴቶች ማብቃት፣ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ በሴቶች አመራር፣ በሰላምና ሀገር ግንባታ እንዲሁም በትውልድ ግንባታ ጉዳዮች ላይ ጥልቀት ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቁመዋል።

‎‎በመድረኩ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮችና ምክትል የቢሮ ሃላፊዎች፣ የአደረጃጀት አመራሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱ ሀገራዊ ንቅናቄውን በመምራት የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አመራሮች ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል።

Please follow and like us: