‎ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ለሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግምታቸዉ ከ5ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ቁሳቁሶችን አስረከበ

ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ለሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር (MoWSA) የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) መሣሪያዎችን በይፋ አስረክቧል።
‎‎ድጋፍ የተደረጉት መሣሪያዎች ሰርቨር ኮምፒውተር (Server) እና ላፕቶፖች ሲሆኑ ዋጋቸው ከ5ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑ በርክክቡ ወቀት ተገልጿል፡፡ ‎ርክክቡ የተፈፀመው በሁለቱ ተቋማት ተወካዮች ሲሆን፣ ድጋፉን የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ተወካይ ወ/ሮ ቅድስት ጌታሁን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሽ ዜጎች ክትትልና ድጋፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ተግይበሉ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል። አቶ ደረጀ በርክክቡ ወቅት ባሰተላለፉት መልዕክት፤ ሚኒስቴሩ በአገር አቀፍ ደረጃ የስደት ተመላሾችን ጉዳይ የማስተባበር ስራ በበላይነት እየመራ እንደሚነኝ ጠቅሰዋል። አሁን የተረከባቸው ቁሳቁሶች በመበልፀግ ላይ ለሚገኘው የየፍልሰት ተመላሾችና መልሶ ማቋቋም መረጃ ቋት አገልግሎት ላይ የሚውል ነው።
‎መረጃ ቋቱ በሚቀጥለው በጀት አመት ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቅሰው መረጃ ቋቱ የመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ስርዓትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተረከባቸውን ቁሳቁሶች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንደሚያውልና አስፈላጊውን ተገቢውን ክትትል እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ‎ወ/ሮ ቅድስት ጌታሁን በበኩላቸው፥ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ለረጅም ጊዜ ከሚኒስቴሩ ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው አረጋግጠዋል።
Please follow and like us: