Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2ሺህ 494 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2ሺህ 2494 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 12 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 312 ወንዶች፣ 163 ሴት እና 19 ጨቅላ ህፃን ሲሆን ከተመላሾች መካከል189 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ96 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ሚኒስቴሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 12 ዙር በረራ የተመለሱት 2ሺህ 312 ወንዶች፣ 163 ሴት እና 19 ጨቅላ ህፃን ሲሆን ከተመላሾች መካከል189 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ96 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ሚኒስቴሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡Please follow and like us:
