በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመግታት የተገቡ ቃል ኪዳኖች አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዩኒሴፍ (UNICEF) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የዝግጅት የምክክር መድረክ በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመግታት እና ከዚህ ቀደም የተገቡ አገራዊ ቃል ኪዳኖችን አፈፃፀም ገምግሞ አጠቃላይ ሪፖርት ለማዘጋጀት ያለመ ነው።

በመድረኩ ላይ የመድረኩን አጠቃላይ አላማና አስፈላጊነት አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት መብትና ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ዘቢደር ቦጋለ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በህፃናት ደህንነት ዙሪያ የገባቻቸውን ቃላቶች አፈፃፀም በዝርዝር ለመገምገም እና የወደፊት ትኩረት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል። በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ በ2026 እ.ኤ.አ የተመዘገቡ ስኬቶች እና የቦጎታ ቃልኪዳን (pledge )አፈፃፀምን ያየ ሲሆን ፣ ከተለያዩ የፌዴራል ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተወካዮችም በትኩረት መስኮቻቸው ዙሪያ ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ግብዐቶች አቅርበው ሰፊ ውይይት እንደሚደረግበት ገልፀዋል።

አያይዘውም በፊሊፒንስ ማኔላ ህዳር 2026 ለሚዘጋጀው የሚኒስትሮች ጉባዔ ተግባራዊ የሚደረጉ አዳዲስ የተነሱ አጀንዳዎችንና ቃልኪዳኖችን በማካተትና ነባሮቹን በማደስና በማካተት የሚቀርቡ ነጥቦችን በትኩረት በመለየት ውይይት እንዲያደርጉና ግብዐት እንዲሰጥባቸው አሳስበዋል።

በመርሃ ግብሩ ውስጥ ከህፃናት ፖርላማ እና ወጣቶች ምክርቤት የተወከሉ አባላትን ጨምሮ የተለያዩ ከመንግስት ሴክተሮች የተጣጣጡ ተሳታፊዎች በቡድን በመደራጀት የቀረቡትን ሪፖርቶች በመገምገም ግብአቶችን በማካተት ውይይት አድርገዋል።የምክክር መድረኩ በውይይቶቹ የተገኙ ምክረ-ሀሳቦችን በማጠናቀር እና የቀጣይ እርምጃዎችን አቅጣጫ በማስቀመጥ ይጠናቀቃል።

Please follow and like us: