Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በእውቀት ላይ የተመሠረተ የዲጂታል ክህሎት — ለነቃ ትውልድና ለጸናች ኢትዮጵያ!
ዓለም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጣን ምጥቀት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ ዕውቀትና የዲጂታል ክህሎት የሀገር ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ መሪዎች ናቸው!
ኢትዮጵያን ወደተሻለ የዕድገት ከፍታ ለማሸጋገር፣ በዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት የበቃ፣ መፍትሔ አመንጪና ንቁ ትውልድ መገንባት የቀደመ ተግባራችን ሊሆን ይገባል።
💡 ለነቃ ትውልድ፦
👉የዲጂታል መሣሪያዎችንና ዕውቀቶችን በመጠቀም የፈጠራ አቅምን ማሳደግ፣
👉በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል መፍጠር ወሳኝ ነው።
🏛️ ለጸናች ኢትዮጵያ፦
👉በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሀገርን የኢኮኖሚ አቅም ማጠናከር
👉በዳጂታል የታገዘ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆኑ አገልግቶችን ለሕዝባችን ማቅረብ
👉የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ጠንካራና በፈተናዎች የማይበገር ሀገራዊ መሠረት መጣል
የእውቀትና የዲጂታል ክህሎት ጉዞ የሁላችንም አሻራ ይፈልጋል! ዛሬ የምንገነባው የዲጂታል አቅም የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ ያረጋግጣልና።
🔗 በዕውቀት እንመራ! በዲጂታል ክህሎት እንበልፅግ! ሀገራችንን እናፅና!
Please follow and like us:
