Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የጀግኖቻችንን ፅናትና ፍቅር የእኛ የሁልጊዜም ሰላም፣ ኩራትና ድል ነው፤ እናመሰግናቸዋለን!
የጀግኖቻችንን ፅናትና ፍቅር የእኛ የሁልጊዜም ሰላም፣ ኩራትና ድል ነው፤ እናመሰግናቸዋለን! 
**************

ሀገር ማለት ከወንዝና ከተራራ በላይ የሰው ልጅ ክብር፣ የማንነት መገለጫና የእናት ያህል መጠጊያ ናት። የዚችን ታላቅ ሀገር ሉዓላዊነት አጽንተው ለማቆየት፣ የሰንደቅ ዓላማዋን ክብር ከፍ አድርገው ለማውለብለብ በቀንና በሌሊት በፅናት የሚቆሙት ጀግኖቻችን የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው። ለሀገር ሰላምና ህልውና ሲሉ መስዋዕትነትን የሚከፍሉ፣ የሀገራቸውን ዳር ድንበርና ህዝብ የሚጠብቁት ሁሉ የወቅቱ ታሪክ ሰሪዎቻችን ናቸው።
ጀግኖቻችንን ማክበር፣ ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና መስጠትና ከጎናቸው መቆም የሁላችንም የዜግነት ግዴታና የሞራል ኃላፊነት ነው።
የእነሱ ፅናትና ፍቅር የእኛ የሁልጊዜም ሰላም፣ ኩራትና ድል ነው። ስለሆነም ለሀገራቸው ወሰንና ሉዓላዊነት በፅናት ለሚቆሙት፣ የሰንደቅ ዓላማችንን ክብር ለሚያስጠበቁት አይበገሬ ጀግኖቻችን ሁሉ የላቀ ምስጋናና ክብር ይድረሳቸው።
—
Please follow and like us:
