Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገው ጥርት ጎን ለጎን ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የመደጋገፍ ተግባር መጠናከር አለበት፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ
መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገው ጥርት ጎን ለጎን ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የመደጋገፍ ተግባር መጠናከር አለበት፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ
*****************
(ታህሳስ 29/2015 ዓ.ም)መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገው ጥርት ጎን ለጎን ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፤ግለሰቦችና ግብረሰናይ ድርጅቶች እጅግ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ ሚኒሰቴር መ/ቤቱ ከኢቢ አካዳሚ ጋር በመቀናጀት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የማዕድ ማጋራትና የድጋፍ መርሃ ግብር ላይ ገልፀዋል፡፡
ክብር ት ሚኒስትሯ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከኢቢ አካዳሚ ት/ቤት ጋር በመተባበር ከ400 በላይ ለሚሆኑ ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች መዓድ ባጋሩበት ወቅት ኢቢ አካዳሚ ያደረገውን በጎ ድጋፍ አመስግነው በቀጣይ ይህንኑ ልምድ ለሌሎች በማጋርት በጎ ድጋፍ የሚያደርጉ አካለትን በማብዛት ችግሮቻችንን በጋራ መቅረፍ እንችላለን ብለዋል፡፡
በመሆኑም ኢቢ አካዳሚ ት/ቤት የገና በዓልን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ዜጎች ጋር በዓሉን እንዲያከብር ከሚ/ር መ/ቤቱ ድጋፍ የተደረገ መሆኑን እና በቀጣይ ይህን መሰል በጎ ስራዎች ለሚሰሩ ድረጅቶች እውቅና ከመስጠት ባሻግር የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ሚኒስትሯ ገልፅዋል፡፡
የሚኒስቴር መ/ቤቱ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሼቴ በበኩላቸው የማህበራዊ ችግሮች ሰፊ በመሆናቸው ከመንግስት ስራ ጎን ለጉን የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች በሚያደርት ትብብር ችግሮችን ለመፍታት ልክ እንደ ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ እንደሚባለው ቢሂል የዜጎቻችንን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ትብብር ዋናው መፍትሄ ነው ብለዋል፡፡
ኢቢ አካዳሚ ት/ቤት አመራሮችም ይህን ዝግጅት ላለፉት 13 ዓመታት ከት/ቤቱ ክበባት መምህራንና የት/ቤቱ ማህበረሰብ በማሰባሰብ የሚያዘጋጁ መሆኑን ገልፀው የዘንድሮውን በዓል ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር ጋር በመተባበር ይህን መሰል ዝግጅት ተዘጋጅቷል ብለዋል።
በመጨረሻም ይህን መሰል ከከፍተኛ የመንግስት አመራሮችና በጎ አድራጎት ማህበር መገኘታቸው ስራችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ከማድረጉም ባሻገር በያዝነው ሀላፊነት ላይ ተጨማሪ አደራን እንድንይዝ ያደርገናል ብለዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ባለሀብቶችና የተለያዩ አከላት ከኢቢ አካዳሚ ት/ቤት ጋር በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡
Please follow and like us:
