Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
1 ሺህ 176 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ በሳኡዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1,176 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1,176 ዜጎች መካከል 1,167 ወንዶች፣ 9 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።
ለተመላሽ ዜጎች በኤርፖርትና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 36,425 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
Please follow and like us:
