933 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ በሳኡዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 933 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 933 ዜጎች መካከል 900 ወንዶች፣ 33 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።
ለተመላሽ ዜጎች በኤርፖርትና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 39,382 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *