Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና ተመላሽ ዜጎች ክትትልና ድጋፍ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ባስተላለፉት መልዕክት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ተዘዋውረው የመስራትና ጥሪት የማፍራት መብታቸው ህገ መንግስታዊና ሰብዓዊ መብት ሆኖ ሳለ መደበኛና ህጋዊ ባልሆነ መልኩ መንቀሳቀስ በተለይም ከአገር ውጭ በተለያዩ ድንበር አሻጋሪ ወንጀለኞች መጓዝ እጅግ ለከፋ ችግር ያጋልጣል ብለዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ዴታዋ አክለውም ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ተመላሽ ዜጎችን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ለአንድ አካል የሚተው ሳይሆን ከፌደራል እስከ ክልል ብሎም እስከታችኛው አደረጃጀት ያሉ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበትና የዜጎችን ችግር መፍታት ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ቢሮ ኃላፋች የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱ በዋነኝነት መደበኛ ባልሆነ የሰዎች ዝውውር መከላከልና ተመላሽ ዜጎች ዙሪያ ያሉ የህግና የአሰራር ማዕቀፎችን ፣የአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጫ መመሪያ ፣የስደት አሉታዊና አውንታዊ ተፅህኖ ፣ የቤተሰብ መሰረት ከስደት ጋር ሊኖረው የሚችለው ተያያዥነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ የእቅድ አፈጻፃፀም እና የቀጣይ ሶስት ዓመታት ዕቅድ የቀረበ ሲሆን በኃላፊዎችና በባለሙያዎች ውይይት ተደርጎበት የተሻለ ግብዓትና አስተያየት ከመድረኩ ማግኘት ተችሏል፡፡
