ሀገር አቀፍ የሕፃናት ጥበቃና የመረጃ አያያዝ ዙሪያ ከክልሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎችና ዳይሬክተሮች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

(ሚያዝያ 17/2015)
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ የህፃናት ጉዳይ አያያዝ ባለሙያዎችና ዳይሬክተሮች አገር አቀፍ የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ ስምምነት፣ ድንጋጌዊችንና ሀገራዊ ህጎችን፣ ፖሊሲና እስትራቴጅ፤ የሕጻናት ጥበቃ ስርዓት በኢትዮጵያ፤ የህጻናት ጥበቃ ጉዳይ አያያዝ፤ የድጋፍና ቁጥጥር ስርዓት፤ ከጥቃት ተጋላጭ የማህበረሰብና ህጻናት ክፍሎች ጋር የመስራት መሰረታዊ ክህሎትና የአቀራረብ ሂደትን አስመልክቶ የሚሰጥ ስልጠና ነው፡፡
ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ህፃናት ጥበቃና ጉዳይ አያያዝና መረጃ ሥርዓት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል።
ይህ ስልጠና በተቋማት መካከል ያለውን የቅንጅት ቅብብሎሽ ክፍተት በመቅረፍ፣ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ጥራት ባለው መልኩ ተደራሽ እንዲሆን የባለሙያዎችን እውቀትና ክህሎት ለማዳበር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
ባለሙያዎች በቀጣይ ስልጠናዎችን እስከታች በማውረድ ለችግር ተጋላጭና ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ህጻናት ከማህበረሰቡ ሳይርቁ በአካባቢቸው ተገቢውን የስነልቦና፣ ማህበራዊና ኢኪኖሚያዊ ድጋፎች እንዲያገኙ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን በመወጣት የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በክልሎች ጠንካራ ስራዎችን ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *