የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር የቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ የከተማ ሴፍቲኔት ድጋፍ እቅድ አፈፃፀም ሁኔታን ገመገመ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት አስፈፃሚ አካላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር የቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ የከተማ ሴፍቲኔትና ድጋፍ እቅድ አፈፃፀም ሁኔታን ገምግሟል።

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያረጉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች በማስተባበር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ከሚያገኙት ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል ።ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በማህበራዊ ሰራተኞች አማካኝነት በሚደረግ የቤት ለቤት ጉብኝትና ኬዝ ማኔጅመንት የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ፍላጎት መግለጫ መረጃዎች በመታገዝ የእህል እና የአይነት ድጋፎችን በመስጠት በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል ።

ሚኒስትር ድኤታዋ አክለውም የፕሮጀክቱን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር የቋሚና ጊዜያዊ ቀጥታ ድጋፍ እቅድ አፈፃፀም ሁኔታን በመገምገም በሂደቱ የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን ለይተን ለማስፋት እና የተስተዋሉብን ጉድለቶቻችን ደግሞ አርመንና ትምህርት ወስደን ዜጎችን በተሻለ ሁኔታ ማገልገል በምንችልበትና የፕሮግራሙን አፈፃፀም ስኬት ወደ ላቅ ደረጃ ማሸጋገር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን አፅንኦት ስጥተዋል፡፡ የፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ማንዋሉ ባስቀመጠው መሰረት ለተጠቃሚዎቻችን አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የተሰጠንን ትልቅ ተቋማዊ ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንድንችል በዓመታዊ እቅዳችን በማካተት ከምናደርጋቸው የአቅም ግንባታ፣ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በተጨማሪ ሴክተራችንን ጨምሮ ስራው በቀጥታ ከሚመለከታቸው ፈፃሚ ተቋማት ጋር በመሆን በማድረግ የትግበራ አቋማችንን መገምገም አንዱና ዋነኛው ነውበ2008 ዓ.ም የተጀመረው የከተማ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያላቸውንና ሌሎች የልዬታ መስፈርቶችን አሟልተው የደሃ ደሃ ተብለው የተለዩትን በቋሚ ቀጥታ ድጋፍ ዘርፍ እንዲሁም ውሎና አዳራቸውን በከተማ ጎዳኖች ላይ ያደረጉ ዜጎችን በልዩ ድጋፍ አገልግሎት ዘርፍ በማካተት የገንዘብና የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ።

በዕለቱ ከፈፃሚ አካላት ወቅቱን የጠበቀ የአፈፃፀም ግምገማ አለመኖር ፣ የመዋቅር አለመጣጣም፣ ከተጠቃሚዎች ቁጥር አንፃር ድጋፉ አሁንም በቂ አለመሆኑ ተነስቶ ምላሽና ማብራሪያ ከሚኒስትር ድኤታዋና ከማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተሰጥቶበታል

Please follow and like us: