Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
370 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 370 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 329 ወንዶች፣ 39 ሴቶች 2 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 16 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን ከ86 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
Please follow and like us:
