የህፃናት አድን ድርጅት ከሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር የህፃናትንና የሴቶችን የአኗኗር ዘይቤ በዘላቂነት ለመቀየር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ ።

ይህ የተገለፀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬና (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የህፃናት አድን ድርጅት አለም አቀፍ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑትን ኡጁ አድረሚን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት የህፃናት አድን ድርጅት ከሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር በሌሎች የህፃናትንና የሴቶችን የአኗኗር ዘይቤና በተለይም በህፃናት ድጋፍና ክብካቤ፣ ያለዕድሜ ጋብቻንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስቀረት ላይ በኢትዮጵያ እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቀዋል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት የህፃናት አድን ድርጅት
ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቀረት እንደሀገር የተዘጋጀው (2020-2024) ፍኖተ ካርታ አካል በመሆንና ግብዓት በመስጠት የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ እና የማህበረሰብ ተሳትፎና ንቅናቄ ስራዎች ላይ በመሳተፍ እንዲሁም ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እስካሁን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ላበረከተው አስተዋፅኦም እውቅና ሰጥተዋል።

በቀጣይ ከድርጅቱ ጋር በማህበራዊ ጥበቃ፣ በማሕበራዊ ጥበቃ ኮንፍረንስ፣ በሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በተለይም በግብርናው ዘርፍ እንዲሠማሩና በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉና በአቅም ግንባታ ዘርፎች፣በቅድመ መደበኛ ትምህርት፣የህፃናት ፓርላማ፣ልዮ ተሰጥኦ ያላቸውንህፃናትና ታዳጊዎች ላይ በትብብር ለመስራት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያለውን ዝግጁነት አስታውቀዋል ።

የህፃናት አድን ድርጅት አለም አቀፍ ፕሮግራም ዳይሬክተር የ ኡጁ አድረሚን በበኩላቸው ድርጀቱ ለተሰጠዉ እውቅና አመስግነው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በህፃናት ድጋፍና ክበካቤ እንዲሁም በሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ላይ እያደረገች ያለችው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይም ድርጅቱ ከሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር የህፃናትንና የሴቶችን የአኗኗር ዘይቤ በዘላቂነት ለመቀየር የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ነገር ግን በቂ ባለመሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ፣ ከሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ተነሳሽነታቸውን ገልፀዋል።

 

Please follow and like us: