የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ባዛር በሐረር ከተማ ተከፈተ

አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ባዛር ዛሬ በሐረር ከተማ ተከፈተ።

በዛሩ አምራች ሴቶች ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት እንደሆነ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል። ባዛሩን የከፈቱት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ እና የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም ናቸው። በሥነ- ሥርዓቱ ላይ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ አመራር አባላት ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Please follow and like us: