አለም አቀፉ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል በሴቶች የተሠሩ የልማት ስራዎችን ተጎበኙ።

የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ114ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!” በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ደረጃ በተለያዩ መርሐግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ የልዑካን ቡድን በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ በሴቶች የተሠሩ የልማት ስራዎችን ጎበኝቷል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኦሮሚያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በዕለቱ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ በተለይ በሴቶች ልማት ህብረትና በግል ጥረታቸው ስራቸውን በመፈጸም ውጤታማ የሆኑ ሴቶችን በመጎብኘት፣ በሴቶቹ የተመረቱ ምርቶችን ኤግዚቢሽንና ባዛር አስጀምረዋል።

እንዲሁም በልማት ህብረት የተሠሩ የግብርና ክላስተር፣ የከብት ዕርባታ፣ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ጎብኝተዋል። 9በዕለቱ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ፣ የተለያዩ ሀገራት ሴት አምባሳደሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ረዳት ሴክሬተሪ ጀነራልን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል ።

 

Please follow and like us: